ሴቶች ዝውውር | አዲስ አበባ ከተማ በአዲስ መልኩ ቡድኑን አዋቅሯል

የመፍረስ አደጋ ተጋርጦበት ዳግም ያንሰራራው አዲስ አበባ ከተማ በቅርቡ አዲስ አሰልጣኝ ከሾመ በኋላ ወደ ዝውውሩ በመግባት ሀያ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ በአዲስ መልክ ቀላቅሏል፡፡

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ የሆነው አዲስ አበባ ከተማ በተደጋጋሚ ሲነሳበት ከነበረው የይፈርሳል ውዥንብር ተርፎ ከአስር ቀናት በፊት ወደ ልምምድ በመግባት ዝግጅቱን ጀምሯል፡፡ ቡድኑ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ማስታወቂያ ማውጣቱ ቢታወስም የክለቡ ቦርድ የማስታወቂያ አወጣጡ አግባብ አለመሆኑን በመግለፅ ዐምና የአሰልጣኝ መሠረት ማኒ ረዳት የነበረችው ሙሉጎጃም እንዳለን በዋና አሰልጣኝነት ከሾመ በኋላ በርካታ ተጫዋቾችን በሙከራ እና በቀጥታ ፊርማ ወደ ቡድኑ በማምጣት በስተመጨረሻ ሀያ ተጫዋቾችን በአዲስ መልክ ሲያስፈርም የአምስት ነባር ተጫዋቾችን ውል ደግሞ አራዝሟል፡፡

ክለቡን የተቀላቀሉ አዳዲስ ተጫዋቾች

ግብጠባቂዎች

ገነት አንተነህ (ኢትዮ-ኤሌክትሪክ)፣ አያንቱ ቶሎሳ (አአ ተስፋ)

ተከላካዮች

ኩሪ አጥቁ (መከላከያ)፣ መልካም ተፈራ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ትበይን መስፍን (ኢትዮ-ኤሌክትሪክ)፣ እምወድሽ አሸብር (ወ/አካዳሚ)፣ ዮርዳኖስ ፍሰሀ (ኢትዮ-ኤሌክትሪክ)

አማካዮች

ጽዮን ሳህሌ (አዳማ ከተማ)፣ አስናቀች ትቤሶ (ልደታ)፣ መዲና ጀማል ( ጥረት ኮርፖሬት)፣ ፍቅርተ አስማማው (ኢትዮ-ኤሌክትሪክ)፣ ዘይነባ ሰዒድ (ኢትዮ-ኤሌክትሪክ)፣ ፍቅርተ ካሣ (ወ/አካዳሚ)፣ ምህረት ተስፋልዑል (ሀዋሳ ከተማ)፣ ማህደር ጋሻው (ኢትዮ-ኤሌክትሪክ)፣ ብፁአት ቹቹ (ድሬዳዋ) ሲቲና ዑስማን (ወ/አካዳሚ)

አጥቂዎች

ስንታየው ማቲዮስ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ዓይናለም መኮንን (አዳማ ከተማ)፣ ምርትነሽ ዮሐንስ (ወ/ አካዳሚ)

ውላቸውን ያራዘሙ

ቱቱ በላይ፣ አሥራት ዓለሙ፣ እታገኝ ሠይፉ፣ ቤተልሄም ሰማን እና ሥርጉት ተስፋዬ


© ሶከር ኢትዮጵያ