የዛሬው ጨዋታ በተያዘለት ሰዓት ይደረጋል

የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የሰበታ ከተማ ጨዋታ በተያዘለት መርሐግብር መሠረት ዛሬ 11:00 በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል።

በቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ወቅት የሁለቱም ክለብ ተወካዮች ባደረጉት ውይይት ጨዋታው መካሄድ እንደሚገባው ከስምምነት በመድረሳቸው እና በተያዘለት ሰዓት ለበዓሉ ማድመቂያ የተሰራው ርብራብ በአግባቡ ፈርሶ እንደሚጠናቀቅ ማረጋገጫ በማግኘታቸው ጨዋታው እንደሚከናወን ታውቋል።

ከፕሪምየር ሊጉ ጨዋታ ቀደም ብሎ በሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ሳምንት አቃቂ ቃሊቲ ከ ሀዋሳ ከተማ በ8:00 ይጫወታሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ