አሰልጣኞች አስተያየት | ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 ሰበታ ከተማ

በ2ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመካሄዱ ነገር አጠራጥሮ የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስና የሰበታ ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ የበላይነት ተጠናቋል። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።

“ይህ ሦስት ነጥብ ለእኛ እጅግ ወሳኝ ነው” ሰርዳን ዝቪጅኖቭ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

“በቅድሚያ ተጫዋቾችን እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ። ጨዋታውን ሙሉ ዘጠና ደቂቃ ተቆጣጥረን መጫወት ችለናል። ተጫዋቾች ከጨዋታው ሙሉ ሦስት ነጥብ ይዘው እንደሚወጡ እምነት ነበረኝ። ይህ ሦስት ነጥብ ለእኛ እጅግ ወሳኝ ነው። ጨዋታው ከጅምሮ ሰበታ ከተማዎች ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች ስለያዙ ከባድ እንደሚሆን ገምተን ነበር። በመጀመሪያ አጋማሽ ብዙ እድሎችን ፈጥረን መጠቀም ባለመቻላችን ስጋት ውስጥ ገብቼ ነበር። ነገርግን በሁለተኛው አጋማሽ በነበረን ነገር አሸንፈን መውጣት ችለናል።”

” እንደ ቡድን ከጨዋታ ጨዋታ መሻሻሎችን እየተመለከትን ነው” ውበቱ አባተ – ሰበታ ከተማ

“እንደ ቡድን ከጨዋታ ጨዋታ መሻሻሎችን እየተመለከትን ነው። ነገርግን እንደ አዲስ እየተገነባ የሚገኝ ቡድን ከመሆኑ አንፃር የሚጠበቅ ቢሆንም አሁንም መሻሻል የሚገባቸው ነገሮች አሉ። በመጀመሪያው አጋማሽ በተለይ የእነሱ አጥቂዎች ከተከላካይ ጀርባ ክፍተቶች የሚፈልጉ እንደመሆናቸው በመጀመሪያ አጋማሽ ያንን እንዳያደርጉ ማድረግ ችለናል። እንደአጋጣሚ ሆኖ ከሽንፈት በኃላ የገጠምነው እጅግ ጠንካራ ቡድን ነው፤ ቢሆንም በፍጥነት ከዚህ የመሸነፍ ስሜት ውስጥ በፍጥነት መውጣት ይኖርብናል።”


© ሶከር ኢትዮጵያ