የጅማ አባ ጅፋር እና የሲዳማ ቡና ጨዋታ የቀን ለውጥ ተደርጎበታል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሦስተኛ ሳምንት የጅማ አባ ጅፋር እና ሲዳማ ቡና ቅዳሜ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ የቀን ለውጥ ተደርጎበታል።

ጅማ አባጅፋር ሦስተኛ ሳምንት ጨዋታውን ነገ ቅዳሜ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ከሲዳማ ቡና ጋር እንዲጫወት አስቀድሞ መርሐግብር ወጥቶለት እንደነበረ ይታወቃል። ሆኖም ባሳለፍነው ረቡዕ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የተጫወተ በመሆኑ፤ አንድ ቡድን ከ72 ሰዓት በፊት እንዳይጫወት በተቀመጠው ደንብ መሠረት የቀን ለውጥ እንዲደረግለት ባቀረበወረ ጥያቄ የሊጉ ዓብይ ኮሚቴ ለውጥ ለማድረግ ተገዷል።

በዚህም መሠረት ቅዳሜ የነበረው ጨዋታ አንድ ቀን ሽግሽግ ተደርጎበት እሁድ ታኀሳስ 5 ቀን በ09:00 በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም የሚጫወት ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ