የአሰልጣኞች አስተያየት | ድሬዳዋ ከተማ 1-0 ሀዲያ ሆሳዕና

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ድሬዳዋ ከተማ በሜዳው ሀዲያ ሆሳዕናን ጋብዞ በሪችሞንድ አዶንጎ ጎል 1-0 ካሸነፈ በኋላ ሰልጣኞቹ በዚህ መልኩ አስተያታቸውን ሰጥተዋል።

“በጫና ውስጥ ሆነን የዛሬውን ጨዋታ አድርገናል” የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ስምኦን ዓባይ

“በፕሪምየር ሊጉ በመጀመሪያዎቹ ጨዋታዎች የደረሱብን ሽንፈቶች ተጫዋቾቼ ላይ ከባድ ጫና ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸው ነበር፡፡ በተለይም ጎንደር ላይ በፋሲል ከነማ የደረሰብን የ 5 ለ 0 ሽንፈት ጫና ውስጥ በሚገባ ከቶን ነበር፡፡ በጫና ውስጥ ሆነን የዛሬውን ጨዋታ አድርገናል፡፡”

” ያገኛቸውን አጋጣሚዎች ባለመጠቀማችን ምክንያት ተሸንፈናል” የሀዲያ ሆሳዕና ም/አሰልጣኝ ኢዘዲን አብደላ

“ያገኛቸውን አጋጣሚዎች ባለመጠቀማችን ምክንያት ተሸንፈናል፡፡ የመጀመሪያው 45ም ሆነ ሁለተኛው አርባአምሰት ፍፁም የተሻልን ነበርን። በቀጣይ በጨዋታ ላይ የሚስተዋሉትን ጥቃቅን ስህተቶች በማሻሻል ለመዘጋጀት የዛሬው ጨዋታ አስተምሮን አልፏል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ