የአዳማ ከተማ ተጫዋቾች የዛሬ ልምምድ አላከናወኑም

የአዳማ ከተማ ተጫዋቾች ከደመወዝ ክፍያ ጋር በተገናኘ ቅሬታ ዛሬ መደበኛ ልምምዳቸውን ሳይሰሩ ቀርተዋል፡፡

አንዳንድ የአዳማ ከተማ ተጫዋቾች ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት ቁጥራቸው ከአስር በላይ የሚሆኑ ነባር ተጫዋቾች ዐምና የግንቦት እና ሰኔ ወር ክፍያ እንዳልተፈፀመ የገለፁ ሲሆን አዳዲስ ክለቡን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች በበኩላቸው ክለቡ የገባልንን ቃል በአግባቡ እየተገበረ አይደለም በሚል ሊያቆሙ እንደቻሉ ገልፀዋል፡፡

የክለቡ ተጫዋቾች ዛሬ ረፋድ ሊሰሩት የነበረውን ልምምድ ያላከናወኑ ሲሆን ከአስር ቀን በፊት በተመሳሳይ ለማቆም አስበው ለክለቡ ደጋፊዎች ክብር በመስጠት እና በቀጣይ ቀናት ክፍያ ይፈፀማል በሚል ተስፋ ሳያቋርጡ ተናግረዋል፡፡

በጉዳዩ ዙርያ የክለቡን ምላሽ እንዳገኘን የምናቀርብ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ