መሐመድ ናስር ዳግም ቡድኑን ተቀላቅሏል

ከ3ኛው ሳምንት በኋላ ከሀዲያ ሆሳዕና ተለይቶ የሰነበተው እና በክለቡ ደብዳቤ የወጣበት አንጋፋው አጥቂ መሐመድ ናስር ከሳምንታት ቆይታ በኋላ ቡድኑን ተቀላቅሎ ልምምድ ጀምሯል።

ቡድኑ ወደ ድሬዳዋ አቅንቶ በድሬዳዋ ከተማ ሽንፈት ካስተናገደ በኃላ ከቡድኑ ተለይቶ የሰነበተው አጥቂው ላለፉት ሁለት ሳምንታት በህክምና ላይ እንደቆየ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር በነበረው አጭር ቆይታ ገልጿል። ” እኔ የውሃ ሽታ አልሆንኩም። ቤተሰብ አለኝ፤ እነሱን ጥዬ የትስ እሄዳለው? የጠፋሁት በጤና ችግር ነው፤ ቡድኑ ማስታወቂያ አውጥቶብኝ ነበር እውነት ነው። ከሶስት ቀናት በፊት ከቡድኑ ጋር ልምምድ ጀምሬያለሁ። አሁን ወደ ሙሉ አቅሜ የተመልስኩ ሲሆን በቀጣይ ጠንክሪ በመጫወት ቡድኔን ማገልገል እጀምራለሁ።” ብሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ