ለ2020 ኢንተርናሽናል ዳኞች የፊፋ ባጅ ተሰጠ

በ2020 የሚደረጉ አህጉር እና ዓለምአቀፍ ጨዋታዎችን የሚመሩ ዳኞች የባጅ ርክክብ በዛሬ ዕለት መከናወኑን ፌዴሬሽኑ በድረ-ገፁ አስታውቋል።

ዛሬ በጁፒተር ሆቴል በተከናወነው ሥነ-ስርዓት 11 ዋና እና 10 ረዳት ዳኞች ከፊፋ የተላከላቸውን ባጅ ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ጂራ የተረከቡ ሲሆን አቶ ኢሳይያስ ጂራም በስፍራው ለተገኙት ዳኞች መልዕክት አስተላልፈዋል።

የ2020 የኢንተርናሽናል ዳኞች ዝርዝር

ወንድ ዋና ዳኞች፡ በዓምላክ ተሰማ፣ በላይ ታደሠ፣ ቴዎድሮስ ምተኩ፣ ብሩክ የማነብርሃን፣ ለሚ ንጉሴ፣ አማኑኤል ኃ/ስላሴ፣ ኃይለየሱስ ባዘዘው

ሴት ዋና ዳኞች፡ ሊዲያ ታፈሰ፣ አስናቀች ገብሬ፣ ጸሀይነሽ አበበ፣ መዳብ ወንድሙ

ወንድ ረዳት ዳኞች፡ ክንዴ ሙሴ፣ ተመስገን ሳሙኤል፣ ትግል ግዛው፣ ሸዋንግዛው ተባበል፣ ፋሲካ የኋላሸት፣ ይበቃል ደሳለኝ

ሴት ረዳት ዳኞች፡ ወይንሸት አበራ፣ ወጋየሁ ዘውዴ፣ ይልፋሸዋ አየለ፣ ብርቱካን ማሞ


© ሶከር ኢትዮጵያ