የሴቶች ከፍተኛ ሊግ | ሻሸመኔ ከተማ ፋሲልን በመርታት ተከታታይ ድል አስመዝግቧል

በሁለተኛ ሳምንት በሴቶች ከፍተኛ ሊግ (ሁለተኛ ዲቪዚዮን) ቅዳሜ ፋሲል ከነማ ከ ሻሸመኔ ከተማ ጎንደር አፄ ፋሲደስ ስታድየም ባደረጉት ጨዋታ ሻሻመኔዎች 2-1 አሸንፈዋል ።

ተመጣጣኝ በነበረው የሜዳላይ እንቅስቃሴ ግብ በማስቆጠር ረገድ ቀዳሚ የነበሩት ሻሸመኔ ከተማዎች ሲሆኑ 17ኛው ደቂቃ ላይ ትሁን ፌሎ ከሳጥን ውጭ ወደ ግብ አክርራ በመምታት ድንቅ ግብ አስቆጥራለች።

በመጀመሪያው አጋማሽ ግቦች ቢቆጠሩም በሙከራ ረገድ ግን የተቀዛቀዙ ነበሩ። 21ኛው ደቂቃ ላይ ከርቀት የተሻገረላትን ኳስ ገፍታ ይዛ በመግባት ከግብ ጠባቂጋር የተገናኘችው ዓለሚቱ ድሪባ ኳሶን ከፍ አድርጋ ከበረኛዋ አናት በለይ ድንቅ ኳስ ብትሞክረውም የኢላማውን የሳተው ኳስ እጅግ የሚያስቆጭ አጋጣሚ ነበር ።

በባለሜዳዎቹ በኩል በመጀመሪያው አጋማሽ በርካታ ጊዜ ወደ ተቃራኒ ግብ ክልል ቢደርሱም አብዛኞቹ አጋጣሚዎች ከጨዋታ ውጭ ነበሩ። 19ኛው ደቂቃ ላይ ዲቦራ ጳውሎስ በጥሩ ሁኔታ ያሻገረችላትን ረድኤት ዳንኤል ሳጥን ውስጥ ያገኘችውን ኳስ በቀጥታ ወደግብ የመታችው ግብ ጠባቂ ያዳነበት ድንቅ ሙከራ ነበር። 36ኛው ደቂቃ ላይ የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ሜላት ንጉሴ ወደግብ በመቀየር ምንትዋቦችን አቻ አድርጋለች ። አንድ ለአንድ በሆነ ውጤትም ወደ እረፍት አምርተዋል።

በሁለተኛው አጋማሽም ሻሸመኔ ከተማዎች በቀኝ በኩል በተደጋጋሚ የጎል አጋጣሚ ለመፍጠር ጥረት ስያደርጉ ተስተውሏል። 70ኛው ደቂቃ ላይም እየሩስ ኤሊያስ ከመሀል ሜዳ ወደ ግብ አክርራ የመታችው ድንቅ ሙከራ ነበር። 86ኛ ደቂቃ ላይም ተቀይራ የገባችው ሜሮን ገይም ከሳጥን ውጭ ያገኘቸውን ኳስ ወደግብ አክርራ በመምታት ድንቅ ግብ አስቆጥራ ብድኗን በድጋሚ መሪ ማድረግ ችላለች ።

በሜዳቸው እንደመጫወታቸው በርካታ ኳሶች ወደ ግብ ቢጥሉም ከመጀመርያው አጋማሽ ስህተቶቻቸውን ያላስተካከሉት ምንትዋቦች ከጨዋታ ውጭ በመሆን በርካታ እድሎችን አምክነዋል። በሙከራ ደረጀ እጅግ የሚያስቆጭ አጋጣሚ የነበረው 88ኛው ደቂቃ ላይ ከግብ ጠባቂ ጋር ተገናኝታ ሳትጠቀምበት የቀረችው አጋጣሚ ነበር።

© ሶከር ኢትዮጵያ