ወላይታ ድቻ ተጫዋቾችን አስጠነቀቀ

ሹም ሽሮችን እያደረገ የሚገኘው ወላይታ ድቻ ለሦስት የቡድኑ ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤን ሰጠ፡፡

የማስጠንቀቂያ ደብዳቤው የደረሳቸው ተጫዋቾች ዘንድሮ ብዙም በክለቡ የመጀመርያ ቋሚነት ዕድል እየሰተሰጣቸው የማይገኙት ተከላካዮቹ ሙባረክ ሽኩር እና ዐወል አብደላ እንዲሁም አጥቂው ሳምሶን ቆልቻ ናቸው፡፡

ክለቡ በተፈለገው ልክ እያገለገሉ አለመሆኑን ገልጾ ልምምድ ለመስራት ፍላጎታቸው እጅጉን የቀዘቀዘ በመሆኑ በአፋጣኝ ራሳቸውን እንዲያርሙ አሳስቧል። በተጨማሪም ዛሬም በቀጠለው ስብሰባ ሌሎች ተጫዋቾችም በቃል ደረጃ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል።

በዘንድሮው የውድድር ዘመን ድሬዳዋ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በተመሳሳይ ለተጫዋቾቻቸው ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው የሚታወስ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: