ወልዋሎ በሁለተኛው ዙር ወደ ሜዳው ይመለሳል

ላለፉት 18 ወራት በእድሳት ላይ የቆየው አንጋፋው የወልዋሎ ስታዲየም ሥራዎቹን በመጠናቀቅ ይገኛል።

በ2010 መጨረሻ የእድሳት ሥራው ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች የተጓተተው ስታዲየሙ ደረጃውን የጠበቀ የመጫወቻ ሳር ጨምሮ የደጋፊዎች መቀመጫ እና መልበሻ ክፍል ያካተተ እድሳት ተደርጎበታል።


በአሁኑ ወቅት የግብ ብረቶች እና ጊዜያዊ የመሮጫ መም እየተሰራለት የሚገኘው ይህ ስታዲየም በዚህ አንድ ወር ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የእድሳት ሥራውን ያጠናቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ ወልዋሎም ከአንድ አመት ስድስት ወር የመቐለ ቆይታ በኃላ ወደ ዓዲግራት የሚመለስ ይሆናል።

ስታዲየሙ በቅርቡ በፕሪምየር ሊጉ ዐቢይ ኮሚቴ ይጎበኛል ተብሎ ሲጠበቅ ምናልባትም ከሁለተኛው የውድድር ዘመን አጋማሽ ጀምሮ ጨዋታዎቹን በሜዳው የሚያከናውን ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ