ሲዳማ ቡና የማበረታቻ ሽልማት ለቡድኑ አባላት አበረከተ

በዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወደ ባለፉት ሳምንታት ወደ ግሩ አቋሙ በመመለስ አንደኛውን ዙር ያገባደደው ሲዳማ ቡና የገንዘብ ሽልማት ተበረከተለት፡፡

ዐምና ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ቡድኑ ዘንድሮ ግን አጀማመሩ ደካማ የነበረ ቢሆንም በጊዜ ሂደት እየተሻሻለ በተለይ ባለፉት አራት የሊጉ የመጨረሻ ሳምንታት ጨዋታ በሰበሰበው ነጥብ ታግዞ ሀያ አራት ነጥቦችን በመያዝ አራተኛ ደረጃን ይዞ የመጀመሪያውን ዙር አጠናቋል፡፡ ቡድኑ በሒደት ላደረገው የውጤት መለወጥ እና መሻሻል አስተዋጽኦ አበርክተዋል ላላቸው የቡድኑ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች እና ሌሎች አባላት ትናንት ምሽት በሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል በተደረገ የእራት ግብዣ የማበረታቻ ሽልማትን አበርክቷል፡፡

በማበረታቻ ሽልማቱ ከሰባት ሺህ ብር ጀምሮ እስከ ሁለት ሺህ ብር የተበረከተ ሲሆን በቀጣይም ቡድኑ በዚሁ ከቀጠለ ዳጎስ ያለ የገንዘብ ሽልማትን እንደሚሰጥ ክለቡ ገልጿል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ