የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዋሳ ከተማ 3-2 ፋሲል ከነማ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 15ኛው ሳምንት ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ በሜዳው ከመመራት ተነስቶ ፋሲል ከነማን 3ለ2 ካሸነፈ በኋላ የሁለቱም ክለብ አሰልጣኞች አስተያየታቸውን እንዲህ ሰጥተዋል፡፡


“እንዲህ እንደሚሆን ጠብቀን ነበር” ረዳት አሰልጣኝ አምጣቸው ኃይሌ (ሀዋሳ ከተማ)

ስለጨዋታው

“ጨዋታውን በጣም በጠበቅነው ልክ ነው ያገኘነው፡፡ እንዲህ እንደሚሆን ጠብቀን ነበር። እኛም በጥንቃቄ ተረጋግተን አሸንፈናል፡፡ በዛሬው ጨዋታ መሐል ላይ ትንሽ ዋዥቀን ነበር፡፡ ጎሉ ከገባብን በኃላ ልጆች ተረጋግተው እንዲጫወቱ ቦታቸውንም ይዘው እንዲያጠቁ አድርገናል። በተለይ ከኋላ ያሉትን ልጆች ጎል ሲገባ ዘርዘር ብለው ነበር፤ በዛም የተነሳ ገብቶብናል፡፡ ያንን አስተካክለን ግን ውጤታማ ሆነናል፡፡

እንደሆንን ያስመሰለን ነበር ” ሥዩም ከበደ (ፋሲል ከነማ)
ስለጨዋታው

“አጀማመራችን የመጀመሪያው አስራ አምስት ሀያ ደቂቃ በኳስ ቁጥጥርም ሆነ ወደ ግብ በመሄድ እኛ የተሻልን ነበርን። በዚህም ደቂቃ ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር ችለናል፡፡ ከዚህም በላይ የምንራመድ ይመስል ነበር፤ ነገር ግን ሁለት ለዜሮ መምራታችን አሸናፊ እንደሆንን ያስመሰለን ነበር። የኛ የመከላከል መላላት ለተጋጣሚ ቡድን ጥንካሬ ሰቷቸዋል፡፡ በእያንዳንዱ ኳስ ትኩረት መስጠት እያለብን በኮንሰንትሬሽን ማጣት ራሳችን የፈጠርናቸው ስህተቶች ዋጋ አስከፍለውናል፡፡ ሀዋሳዎች ሁለት ለዜሮ እየተመሩ ከኋላ ተነስተው ያደረጉት ጥረት ቀላል የሚባል አልነበረም፡፡ በራሳችንን ስህተቶች ዋጋ ከፍለናል። ከእረፍት በኋላ ጥሩ ለመጫወት ሞክረናል። በአጠቃላይ ግን ለኛ ጨዋታው ደስታን የፈጠረ አይደለም፡፡ ይህ ብዙ ነገር አበላሽቶብናል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ