የፕሪምየር ሊጉ ሁለተኛው ዙር የሚጀምርበት ቀን ታውቋል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ የውድድር ዘመን አጋማሽ የሚጀምርበት ወቅት ላይ የሊጉ ዐቢይ ኮሚቴ ከውሳኔ ደርሷል።

የሊጉ አንደኛ ዙር ዛሬ በተካሄደ ጨዋታ መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን ሁለተኛው ዙር የሚጀምርበት ቀን ባለመገለፁ ምክንያት የተለያዩ መረጃዎች እና መላምቶች ሲወጡ ቆይተዋል። በተለይም የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች የሚደረጉበት ጊዜ ከመቃረቡ ጋር ተያይዞ ለዝግጅት ሰፋ ያለ የእረፍት ቀናት ይኖራል ወይስ በቶሎ ውድድሩ ይጀምራል የሚለው መነጋግርያ ሆኖ ቆይቷል። ዛሬ ስብሰባ የተቀመጠው የሊጉ ዐቢይ ኮሚቴም ከ2 ሳምንታት በኋላ እንዲጀምር ወስኗል። ይህም ማለት የካቲት 29 እና 30 ቀን 2012 ነው።

ከሊጉ ጋር የተያያዙ ተጨማሪ መረጃዎችን ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

error: