ሀዲያ ሆሳዕና ለሁለተኛ ጊዜ የዲሲፕሊን ቅጣት ተላልፎበታል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 16ኛው ሳምንት ሀዲያ ሆሳዕና በመቐለ 70 እንደርታ በሜዳው 1ለ0 ሲሸነፍ በተከሰተው የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት ለሁለተኛ ጊዜ ቅጣት ተላልፎበታል፡፡

በ16ኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታ በሜዳው በመቐለ 70 እንደርታ ቡድኑ 1ለ0 ሲሸነፍ በተነሳው የደጋፊዎች ተቃውሞ ቁሶች ወደ ሜዳ በመወርወራቸው እና የመቐለ የህክምና ባለሙያም የመፈንከት አደጋ የገጠመው በመሆኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሀዲያ ሆሳዕናን ጥፋተኛ በማለት አምስት የሜዳውን ጨዋታዎች ከሜዳው ውጪ እንዲጫወት እንዲሁም ደግሞ 110 ሺህ የገንዘብ ቅጣት ተላልፎበታል፡፡ በዚህም ከዚህ ቀደም የሁለት ጨዋታ ቅጣት በተላለፈበት ወቅት በተጫወተበት ሀዋሳ ቅጣቶቹን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡

ቅጣቱን ተከትሎ ሀዲያ ሆሳዕና በ2012 የውድድር ዘመን በሜዳው አቢዮ ኤርሳሞ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች በ27ኛው እና 29ኛው ሳምንት ከሰበታ እና ሽረ ጋር ብቻ የሚያከናውናቸው ይሆናሉ። 

ዝርዝር ደብዳቤ


© ሶከር ኢትዮጵያ