ሀዋሳ ከተማ ሥራ አስኪያጁን ከኃላፊነት አንስቷል

ሀዋሳ ከተማን ለረጅም ዓመታት በሥራ አስኪያጅነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ጠሀ አህመድ ተሰናብተው አንዱአለም አረጋ በጊዜያዊነት ተሹሟል፡፡

ሀዋሳ ከተማ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ክለቡን ከሰባት ዓመታት በላይ በዋና ሥራ አስኪያጅነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ጠሀ አህመድን ለማሰናበት ከውሳኔ ላይ መድረሱ ታውቋል። በምትኩም ክለቡን በተጫዋችነት አሁን ደግሞ በፀሀፊነት እያገለገለ የሚገኘው እንዲሁም ለረጅም ዓመታት የዋናውን ቡድን ጨምሮ በክለቡ ስር ያሉ ቡድኖች ውስጥ በቡድን መሪነት ሲሰራ የነበረው አቶ አንዱዓለም አረጋ በጊዜያዊ ሥራ አስኪያጅነት ከፀሀፊነቱ ጋር በጋራ አድርጎ እንዲሰራ ተመድቧል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ