የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ማኅበር ድጋፍ የማሰባሰብ ተግባር ነገ ፍፃሜውን ያገኛል

የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ማኅበር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አቅመ ደካሞች እና የጎዳና ተዳዳሪዎች ችግር ውስጥ እንዳይገቡ በማሰብ ያሰባሰበውን ገንዘብ እና ቁሳቁሶችን ነገ ሊያስረክብ ነው።

የኮሮና ወረርሽኝ በዓለም እና በሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ ቀውስ ከመፍጠሩ ባሻገር በስፖርቱ ረገድም በውድድሮች እና ስልጠናዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ በመፍጠር ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ያስቆመ ተግባር መሆኑ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ የኢትዮዽያ ተጫዋቾች ማኅበር ማኀበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በማሰብ አባላቱ እና የስፖርት ቤተሰቡ አቅም በፈቀደ መጠን ለአቅመ ደካሞች፣ ለጎዳና ተዳዳሪዎች ይውል ዘንድ እርዳታ የማሰባሰብ ዕቅድ አውጥቶ የገንዘብ፣ የምግብ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ለቀናት ሲያሰባስብ መቆየቱ ይታወሳል። የዚህ በጎ አላማ ማጠቃለያና ነገ (አርብ ሚያዚያ 9) ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚመለከተው አካል የርክክብ መርሐ ግብር እና የነበረውን ሂደት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ አዘጋጅቷል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ