የድሬዳዋ የስፖርት ተቋማት ድጋፍ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል

የድሬዳዋ ከተማ የወንዶች ቡድን የአንድ ወር ሙሉ ደሞዛቸውን በመለገስ የተጀመረው መልካም ተግባር በሌሎች የስፖርት ተቋማትም ቀጥሏል።

በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል እና አቅመ ደካሞችን ለመርዳት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ በቀጠለበት በዚህ ጊዜ የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን በዛሬው ዕለት ግምቱ ሦስት መቶ ሺህ ብር የሚያወጣ የምግብ እህል እና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል። በተመሳሳይ የድሬዳዋ ዳኞች እና የጨዋታ ታዛቢዎች (ኮሚሽነሮች) የሙያ ማኀበር የ15 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

ከሰሞኑ የድሬዳዋ የወንዶች ቡድን ከአንድ ሚልየን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ የወር ደሞዛቸውን በመስጠት የጀመረው ልግስና በሴቶች ቡድኑ፣ በክለቡ የደጋፊዎች ማኀበር አማካኝነት ቀጥሎ የገንዘብ፣ የቁሳቁስ እየተደረገ ይገኛል። በከዚህ በተጨማሪ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች በድሬደዋ አካባቢዎች በመዟዟር የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብሮችን እያደረጉ መሆኑን ሰምተናል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ