ፋሲል ከነማ በቴሌግራም እና ቪዲዮ ኮንፈረንስ ከቡድን አባላቶቹ ጋር ግንኙነት ጀምሯል

ፋሲል ከነማዎች የተጫዋቾችን የቡድኑን መንፈስ ለማነቃቃት የቴሌግራም ግሩፕ እና የቪዲዮ ኮንፈረንስ ጀምረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከተቋረጠ በርካታ ሳምንታትን አስቆጥሯል። ይህን ተከትሎም ክለቦች የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም አባላቶቻቸውን በማሰባሰብ እና ልምምድ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብም በቴሌግራም ግሩፕ በመክፈት ተጫዋቾችን እና የአሰልጣኞችን ስታፍ ያመከለ ስራ እየተሰራ መሆኑን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። ክለቡ በቴሌግራም ግሩፕ እና በቪዲዮ ኮንፈረስ የጀመረው ተግባር የተጫዋቾች እና የአሰልጣኞች ቡድኑን አብሮነት ለማጠናከር እንዲሁም የቡድን መንፈሱን ለማስጠበቅ የሚደረግ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን ተጫዋቾች የየግላቸውን ተሞክሮ የሚያካፍሉበት እንዲሁም አሰልጣኞች እግርኳስ ነክ ትምህርቶችን የሚያስተላልፉበት ግሩፕ መከፈቱን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ