የተጫዋቾች ማኅበር ለስድስት የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ምስጋና አቀረበ

አስቀድሞም የፋይናስ ቀውስ እንዳለባቸው ቢገመትም የኮሮና ቫይረስ ችግር ተጨምሮበት ስድስት የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ለተጫዋቾች ደሞዝ በመክፈላቸው ማኅበሩ ምስጋና አቅርቧል።

ምስረታውን በቅርቡ ካደረገበት ማግስት አንስቶ የተለያዮ መልካም ተግባሮች እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ማኀበር ባወጣው መግለጫ የኮሮና ቫይረስ የሰዎችን እንቅስቃሴ የገደበ እና ኢኮኖሚዊ ቀውስ እያስከተለ መምጣቱ ይታወቃል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንም ውድድር መሠረዙና የተጫዋቾች ደሞዝ በውላቸው መሠረት እንዲከፈላቸው ማሳሰቡ ይታወሳል ያለው ማኅበሩ ይህን ተከትሎ ሰባት ክለቦች ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ድሬደዋ ከተማ፣ ባህር ዳር ከተማ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና ሲዳማ ቡና ከከፍተኛ ሊግ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ይህንን የተጫዋቾች የደሞዝ ክፍያ እየፈፀሙ በመሆናቸው እና ሌሎችም ክለቦች ክፍያውን ለመፈፀም በሂደት ላይ በመሆናቸው ማኀበሩ ምስጋና አቅርቧል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ