ሦስት ክለቦች የተጫዋቾች ደሞዝ የከፈሉ ቀጣይ ክለቦች ሆነዋል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተጫዋቾችን ደሞዝ የከፈሉ ቡድኖች አስር የፕሪምየር ሊግ ክለቦችን ጨምሮ 16 ሲደርሱ ማኅበሩ በዛሬው ዕለት ሁለት የፕሪምየር ሊግ ክለቦችን አመስግኗል።

የኮሮና ቫይረስ ምክንያት የ2012 ውድድር መሠረዙ ተከትሎ ክለቦች የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የተጫዋቾች ደሞዝ በውላቸው መሠረት እንዲከፈላቸው ባሳሰበው መሠረት ይህን በማክበር ወልቂጤ ከተማ፣ ሰበታ ከተማ እና የከፍተኛ ሊጉ ተሳታፊ ነቀምት ከተማ የተጫዋቾች የደሞዝ ክፍያ የፈፀሙ በመሆናቸው ማኀበሩ ምስጋና አቅርቧል።

ማኅበሩ እስካሁን ባሰራጨው መረጃ መሠረት ወላይታ ድቻ፣ ወልዋሎ፣ አዳማ ከተማ፣ ሀዲያ ሆሳዕና፣ ስሑል ሽረ፣ ጅማ አባ ጅፋር የተጫዋቾች ደሞዝ ስለመክፈላቸው ያልተጠቀሱ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ሆነዋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ