የኢትዮጵያውያን አሰልጣኞች ከፊፋ ጋር ዛሬ ረፋድ በዙም አማካኝነት የቪዲዮ ኮንፍረንስ አደረጉ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከፊፋ ጋር በመነጋገር ዛሬ ረፋድ ላይ በርከት ያሉ አሰልጣኞች የተካፈሉበት ውይይት በዙም (Zoom) አማካኝነት አድርገዋል።

ለአርባ ደቂቃ በፈጀው በዚህ ስልጠና ላይ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ ፣ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የወቅቱ አሰልጣኝ አብርሐም መብራቱ፣ የቴክኒክ ኮሚቴው ኃላፊ መኮንን ኩሩ፣ አሰልጣኝ አብርሐም ተክለሐይማኖት፣ አንጋፋው አሰልጣኝ ጋሽ ከማል እና በታዳጊ ቡድኖች ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ ብዛት ያላቸው አሰልጣኞች በኮንፈረሱ ላይ ተካፋይ ሆነውበታል።

ዘጠኝ ሰዓት በጀመረው በዚህ ስልጠና ፊፋን በመወከል Jose Ramon Capdevila (ከስፔን) በዋናነት የስልጠናቸው ትኩረት ያደረገው ኢትዮጵያ የታዳጊ ፕሮጀክቶችን የአሰለጣጠን መንገዷ በምን መልኩ ቢሆን ሀገር ሊያሳድግ ይችላል። እንዴት ተደርጎ ነው የተሻሉ ተፎካካሪ ተጫዋቾችን በማውጣት ለብሔራዊ ቡድን ማድረስ የሚቻለው እና የሀገሪቱን እግርኳስ ለማሳደግ እንዴት ማሻሽል እንደሚቻል የዛሬው ስልጠና የተመለከታቸው ነጥቦች ናቸው።

በቀጣይ ከ15 ቀን በኃላ በተመሳሳይ በዚሁ የታዳጊዎች ስልጠና ዙርያ ኮንፍረሱ እንደሚቀጥል ለማወቅ ችለናል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ