የተጫዋቾች ማኀበር የአቋም መግለጫ አወጣ

ለወራት በሁሉም ውድድሮች የተጫዋቾች ደሞዝ ሳይከፈላቸው መዘግየቱን አስመልክቶ የተጫዋቾች ማኀበር የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

እንደ ማኀበሩ ገለፃ ከሆነ የፕሪምየር ሊግ፣ የከፍተኛ ሊግ፣ የአንደኛ ሊግ፣ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ቡድኖች ያልከፈሉትን ደሞዝ እስከ ሐምሌ አምስት ድረስ ከፍለው እንዲያጠናቅቁ ፌዴሬሽኑ ያወጣውን መመርያ ማኀበሩ የሚያከብር መሆኑን አሳውቆ። ከሐምሌ አምስት በኃላ ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን ተግባራዊ የማያደርግ ከሆነ የአባሎቹን መብት ለማስከበር ሲል በህግ አግባብ የሚሄድበት መሆኑን በዛሬው መግለጫ አሳውቋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ