ሳሙኤል ዮሐንስ ወደ ዐፄዎቹ አምርቷል

ፋሲል ከነማ ሁለገቡ ሳሙኤል ዮሐንስን የግላቸው አድርገዋል።

የነባሮች በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም የተጠመዱት ፋሲል ከነማዎች አሁን ደግሞ ከወልዋሎ ጋር ጥሩ ዓመት ያሳለፈው የመስመር ተከላካዩ ሳሙኤል ዮሐንስን አስፈርመዋል። በወልዋሎ የአንድ ዓመት ቆይታው ቡድኑን በአምበልነት ጭምር በመምራት በተለያዩ ቦታዎች በመሰለፍ የተጫወተው ይህ የግራ መስመር ተከላካይ ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር እየተነሳ ቢቆይም በመጨረሻው ማረፍያው በዐፄዎቹ ቤት ሆኗል።

በእግር ኳስ ሕይወቱ ለአውስኮድ፣ ንግድ ባንክ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ወልዋሎ የተጫወተው ይህ ተከላካይ ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ብሔራዊ ቡድንም ተሰልፎ ተጫውቷል። ከሰዓታት በፊት ለዐፄዎቹ ቅድመ ኮንትራት የፈረመው ሳሙኤል ለቋሚነት ከአምሳሉ ጥላሁን ጋር ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል ተብሎ ይገመታል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ