ወላይታ ድቻ አዲስ ሥራ አስኪያጅ ሾመ

ክለቡ ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሰረት ሲቪያቸውን አስገብተው ሲወዳደሩ ከነበሩ ግለሰቦች መካከል አቶ ኢያሱ ነጋ አዲሱ የክለቡ ስራ አስኪያጅ ሆነው ተመርጠዋል።

ወላይታ ድቻ ባለፉት ወራት የክለቡን ስራ አስኪያጅ ለመቅጠር ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል። ይህንን የክለቡ የቅጥር ማስታወቂያ ተከትሎ ሲቪያቸውን ያስገቡ 20 ተወዳዳሪዎች ዛሬ ውጤታቸው መታወቁን ክለቡ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት አቶ ኢያሱ ነጋ ማግኘት ከነበረባቸው 100 ነጥቦች 92ቱን በማግኘት አዲሱ የክለቡ ስራ አስኪያጅ ሆነው ተመርጠዋል። እስካሁን በዝውውር ገበያው ተሳትፎ እያደረገ ያልነበረው ክለቡ በቀጣይ የነባር ተጫዋቾቹን ውል በማደስ ስራውን አጠናክሮ እንደሚጀምር አስታውቋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ