ኢትዮጵያ ቡና ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል

የኢትዮጵያ ቡና እግርኳስ ክለብ ነገ ረፋድ ላይ በክለቡ ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጥ ነው።

ሜክሲኮ በሚገኘው በክለቡ ፅፈት ቤት አዳራሽ በ08:00 በሚሰጠው በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በዋናነት በነሐሴ ወር ይካሄዳል ተብሎ በሚታሰበው የቤተሰብ ሩጫ ዙርያ፣ በክለቡ ወቅታዊ ሁኔታ ዙርያ እና ተያያዥ ጉዳዮች አስመልክቶ ለጋዜጠኞች ዝርዝር ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: