ባህር ዳር ከተማ የአማካዩን ውል አራዝሟል

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት የጣና ሞገዶቹ ከደቂቃዎች በፊት የአንድ ተጫዋች ውል አድሰዋል።
የበርካታ ነባር ተጫዋቸችን ውል እያደሱ የሚገኙት የጣናው ሞገዶቹ የሳምሶን ጥላሁንን ውል ለተጨማሪ 2 ዓመታት ማደሳቸው ታውቋል። በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ያደገው እና አንድ ዓመት በቡድኑ ተጫውቶ ያሳለፈው ሳምሶን በ2006 ክለቡን ለቆ ወደ ደደቢት ማምራቱ ይታወሳል። በደደቢት ጥሩ ጊዜ በማሳለፍ በ2010 ወደ ኢትዮጵያ ቡና ያመራው ተጨዋቹ በቡናማዎች ቤት ጥሩ ጊዜ ማሳለፉ ይታወሳል። በዘንድሮ የውድድር ዘመንም ወደ ባህር ዳር በማምራት የፋሲል ተካልኙን ክልብ ሲያገለግል ቆይቷል።

የጣና ሞገዶቹ ከዚህ በፊት የፍቅረሚካኤል ዓለሙ፣ የዜናው ፈረደ፣ የደረጄ መንግስቱ፣ የኃይለየሱስ ይታየው፣ የአቤል ውዱ፣ ወሰኑ ዓሊን እና ሚኪያስ ግርራን ውል ለተጨማሪ 2 ዓመታት ማደሳቸው አይዘነጋም።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: