ጅማ አባጅፋር አዲስ የክለቡ የበላይ ጠባቂ አገኘ

የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋቾች፣ የክለቡ አመራሮች እና ደጋፊዎች እጅግ ተስፋ የጣሉባቸው አዲስ የበላይ ጠባቂ ወደ ክለቡ መጥተዋል።

ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአደገበት ዓመት የሊጉን ዋንጫ ካነሱ ሁለት ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው ጅማ አባጅፋር በተለያዩ ውስብስብ ችግሮች ምክንያት የክለቡ ህልውና ጥያቄ ውስጥ መግባቱ ይታወቃል። አሁን ካለበት ጊዜያዊ ችግር ተላቆ ክለቡ ህዝባዊ መሰረቱን ጠብቆ መዝለቅ እንዲችል በብዙዎች እምነት የተጣለባቸው አዲስ የበላይ ጠባቂ ወደ ክለቡ መጥተዋል።

የጅማ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ከንቲባ ሆነው የተሾሙት አቶ ትጃኒ ናስር (የክለቡ የበላይ ጠባቂ) ባሳለፍነው ሳምንት ጅማ
ከሚገኙ ተጫዋቾች እና የክለቡ አባላት ጋር ሰፊ ውይይቶችን አድርገዋል። በዚህም ውይይት ክለቡ የነበረበትን ጊዜያዊ ችግር ከገመገሙ በኃላ የከተማው አዲስ ከንቲባ በመሆን የተሾሙት አቶ ትጃኒ ናስር በከተማው ህዝብ የሚወደደውን ክለብ ወደ ነበረበት ከፍታ ለመመለስ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ እንደሚያደርጉ እና በቅርቡ ያሉት ችግሮች በማስተካከል ክለቡን በተጠናከረ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማድረግ የሚችሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

በሁሉም የጅማ ስፖርት ቤተሰብ ተስፋ የተጣለባቸው አዲሱ የከተማው ከንቲባ በቅርቡ ተጨማሪ ውይይቶችን ክለቡ ጋር ግንኙነት ካላቸው አካላት ጋር በመምከር ወደ ስራ እንደሚገቡ ለማወቅ ችለናል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ