ወላይታ ድቻ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማምቷል

የጦና ንቦቹ ሰዒድ ሀብታሙን ወደ ክለቡ ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

ከአንድ ቀን በፊት አራት ወጣት ተጫዋቾችን አስፈርመው የነበሩት ወላይታ ድቻዎች አሁን ደግሞ አምስተኛ ተጫዋቹን ለማስፈረም የቃል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል። ግብ ጠባቂው ሰዒድ ሀብታሙ በሁለት ዓመት ውል ለመቀላቀል ነው የተስማማው፡፡ አርባምንጭ ከተማን በተሰረዘው ዓመት ለቆ ወደ ጅማ አባጅፋር አምርቶ ዘንድሮ በሊጉ ከታዩ ምርጥ ግብ ጠባቂዎች መካከል አንዱ እንደነበር ይታወቃል።

ክለቡ በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ ግብ ጠባቂን ጨምሮ አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም በሒደት ላይ መሆኑን ሰምተናል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: