መቐለ 70 እንደርታ ግብ ጠባቂ አስፈረመ

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያለውን ውል ያጠናቀቀው በረከት አማረ ወደ መቐለ አምርቷል።

የእግርኳስ ሕይወቱን በወልዋሎ ጀምሮ ወደ አውሥኮድ በማምራት የቋሚነት ዕድል ያገኘው ይህ ግብ ጠባቂ ወደ አሳዳጊ ክለቡ ተመልሶ በቆየባቸው ዓመታትም የተሳኩ ጊዜያት አሳልፎ ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል። የተሰረዘውን የውድድር ዓመት ደግሞ በኢትዮጵያ ቡና ከተ/ማርያም ሻንቆ ጋር በመፈራረቅ ሲጫወት ቆይቷል።

ቀደም ብለው ከፍሊፕ ኦቮኖ ጋር የተለያዩት መቐለዎች ከሦስት ዓመታት በኃላ ያለ የውጭ ሀገር ግብ ጠባቂ ሊጉን የሚጀምሩ ሲሆን ከክለቡ ጋር በአንድ ዓመት ውል የተስማማው በረከት አማረም ለቋሚ ተሰላፊነት ከሶፎንያስ ሰይፈ እና ምሕረትአብ ገብረህይወት ጋር የሚፎካከር ይሆናል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ