ጅማ አባ ጅፋር እገዳ ተጣለበት?

ጅማ አባጅፋር ከጋናዊው ግብጠባቂ ዳንኤል አጄይ ደሞዝ አለመከፈል ጋር በተያያዘ በፊፋ ጠንከር ያለ እገዳ እንደተላለፈበት በአፍሪካ እግርኳስ ላይ የሚያተኩረው ጋና ሶከርኔት ዘግቧል።

እንደ ድረ-ገፁ ዘገባ ከሆነ ጅማ አባ ጅፋሮች ለሁለት የውድድር ዓመታት የክለባቸውን ማልያ ለብሶ የተጫወተው ግብጠባቂን ደሞዝ ባለመክፈላቸው ለሦስት የዝውውር መስኮቶች እገዳ ተጥሎበታል። በአፕሪል 15 የተጫዋቹን ደሞዝ እንዲከፍሉ ውሳኔ የተሰጠባቸው ጅማዎች ውሳኔውን የማይቀበሉ ከሆነ የሰነድ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ቢጠየቁም እስካሁን ድረስ እንዳላቀረቡ የገለፀው ድረ-ገፁ ክለቡ እግዱ እንዲነሳለት የተጫዋቹን ደሞዝ መክፈል እንደሚጠበቅበትም ገልጿል።

ስለ ጉዳዩ ሃሳባቸው የሰጡት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁንም ፅህፈት ቤታቸው ከዳንኤል አጄይ ክስ ጋር በተያያዘ የቀረበለት ነገር እንደሌለ እና ስለጉዳዩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልፀውልናል። በቀጣይም የጅማ አባጅፋር አመራሮች ሃሳብ ይዘን ለመቅረብ ጥረት እናደርጋለን።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: