አዳማ ከተማ የሁለት ተጫዋቾች ውል ለማራዘም ተስማማ

ሚካኤል ጆርጅ እና ዱላ ሙላቱ ከአዳማ ከተማ ጋር ለመቀጠል ተስማሙ።

ከዚ ቀደም በሙገር ሲሚንቶ፣ ሲዳማ ቡና፣ ደደቢት እና አውሥኮድ የተጫወተው ግዙፉ አጥቂ ሚካኤል ጆርጅ ባለፈው ዓመት በድጋሚ ወደ አዳማ ከተመለሰ በኃላ ተቀይሮ እየገባ ቡድኑ ማገልገሉ ይታወሳል።

የቀድሞው የነቀምቴ ከተማ፣ ሀዲያ ሆሳዕና እና መቐለ 70 እንደርታ ፈጣን የመስመር አጥቂ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በአዳማ ከተማ ያሳለፈ ሲሆን እንደ ሚካኤል ሁሉ ተቀይሮ እየገባ ቡድኑን አገልግሏል።

አዳማ ከተማዎች እስካሁን ድረስ አምስት ተጫዋቾች ለማስፈረም ሲስማሙ የሦስት ተጫዋቾች ውል ለማራዘምም ቅድመ ስምምነት አድርገዋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: