ሲዳማ ቡና የወሳኙን አማካይ ውል አራዘመ

ዛሬ በውል ማደስ እና አዲስ ተጫዋቾች በማስማማት ተጠምደው የዋሉት ሲዳማ ቡናዎች የአጥቂ አማካዩ ዳዊት ተፈራን ለመቆየት ተስማምተዋል፡፡

ሲዳማ ቡና ከ2011 ጀምሮ ለአማካይ ክፍሉ ጥንካሬ ተጠቃሽ ከሆኑ ተጫዋቾች አንዱ የነበረው የቀድሞው የጅማ አባቡና የአጥቂ አማካዩ ዳዊት ተፈራ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ በሰፊው ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ስሙ ቢያያዝም በስተመጨረሻም ለሁለት ተጨማሪ ዓመታት በሲዳማ ቡና ቤት ለመቆየት ተስማምቷል፡፡

ዳዊት ተፈራን ጨምሮ ውል ያራዘሙ ተጫዋቾች ቁጥር ወደ አስራ አራት የደረሰ ሲሆን ለመቀላቀል የተስማሙት ቁጥር ደግሞ አራት ደርሷል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!