የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በጎርፍ አደጋ ለተፈናቀሉ የአፋር ክልል ነዋሪዎች ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ በተገኙበት ለተፈናቀሉ የአፋር ማኅበረሰብ የሦስት መቶ ሺህ ብር የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍን አድርገዋል፡
በቅርቡ በአፋር ክልል የአዋሽ ወንዝ በጎርፍ ምክንያት በመሙላቱ የተነሳ የአካባቢው ማኅበረሰብ ከመኖሪያ ቅያቸው ለመፈናቀል የተደገዱ ሲሆን ንብረታቸውም በጎርፍ መወሰዱ ይታወሳል፡፡ እነኚህን ከአካባቢው የተፈናቀሉትን ማኅበረሰብን በስፖርቱ ዘርፍ ያሉ አካላት ድጋፍ እያደረጉ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ለተፈናቃዮቹ ለግሷል፡፡ 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ እና የሥራ አስፈፃሚ አባሉ አቶ አሊሚራህ መሀመድ በተገኙበትም የሦስት መቶ ሺህ ብር የገንዘብ እና የተለያዩ የአልባሳት ድጋፍን በስፍራው በመገኘት ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በፌዴሬሽኑ ስም በይፋ ማበርከቱን ኑር ከዳባ ከሰመራ ለሶከር ኢትዮጵያ ያደረሰው መረጃ ይጠቁማል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!