የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሊሸጥ ነው

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አ/ማ የፕሪምየር ሊግ ውድድርን በቴሌቭዥን ማስተላለፍ ለሚችሉ የሚዲያ ተቋማት ሊሸጥ መሆኑ ታውቋል፡፡


(መረጃው የኢፊዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ነው)

በሀገራችን የሚካሄደው የወንዶች እግር ኳስ የፕሪምየር ሊግ ውድድር በ16 ክለቦች መካከል በሜዳ እና ከሜዳ ውጭ በሚል የውድድር ፎርማት ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም ሊግ ካምፓኒው በቀጣይ የሚካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት የማስተላለፍ ፍቃድ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ የሚዲያ ተቋማት ለመሸጥ ጫራታ ሊያወጣ መሆኑ ተሰምቷል ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ሊግ ካምፓኒው የፕሪምየር ሊግ ውድድሩን ስም ለመሸጥ በሚቀጥለው ሳምንት ጨረታ እንደሚያወጣ ለማወቅ ተችሏል ፡፡ ሊግ ካምፓኒው ከቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት እና ከውድድር ስያሜ ሽያጭ የሚያገኘው ገቢ የካምፓኒውን እና የተወዳደዳሪ ክለቦችን ፋይናንሻል አቅም ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል።


“ሊጉን በቴሌቪዥን ለማስተላለፍ በመስከረም ወር ጨረታ እናወጣለን” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ | Link


© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!