ድሬዳዋ ከተማ ከአንበሉ ጋር ሊለያይ ነው

ያለፉትን አራት ዓመታት አመዛኙን ጨዋታ በመጫወት ድሬዳዋ ከነማን በማገልገል የሚታወቀው ግብጠባቂው ሳምሶን አሠፋ ከክለቡ ጋር ሊለያይ ተቃርቧል።

ለቀጣይ ዓመት ራሱን ለማጠናከር አዳዲስ ተጫዋቾችን በማምጣት እና የነባር ተጫዋቾችን ውል በማራዘም ላይ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ከአንጋፋው ግብጠባቂ ጋር የመለያየታቸው ምክንያት ምን እንደሆነ በውል ባይታወቅም እስካሁን ክለቡ በውል ማራዘም አለማራዘም ጉዳይ ንግግር አለማድረጋቸው እና እስካሁን ሦስት ግብ ጠባቂዎች በማስፈረሙ እና ውል በማራዘሙ የመለያየታቸው ነገር ዕውን የሆነ ይመስላል።

ሳምሶን ያለፉትን አራት ዓመታት ቡድኑን በጥሩ ብቃት ከማገልገሉ በተጨማሪ በአንበልነት ቡድኑን እየመራ መቆየቱ ይታወቃል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ