መቐለ 70 እንደርታዎች ሁለገቡን ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ

ሰለሞን ሀብቴ ወደ መቐለ 70 እንደርታ ለማምራት ተስማምቷል።

በግራ መስመር ተከላካይነት እና በአማካይነት መጫወት የሚችለው ሰለሞን ከሁለት ዓመት በፊት ከደደቢት ከተለያየ በኃላ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በዐፄዎቹ ቤት አሳልፏል። በ2008 ወደ ወላይታ ድቻ አምርቶ ለአንድ የውድድር ዓመት የጦና ንቦች ማልያ ለብሶ ከተጫወተበት አንድ ዓመት ውጭ ለተከታታይ ዓመታት በደደቢት የተጫወተው ሰለሞን ለግራ መስመር ተከላካይ ቦታ ቋሚ ተሰላፊነት ከሳምንታት በፊት ውሉን ካራዘመው አንተነህ ገብረክርስቶስ የሚፎካከር ይሆናል። በአራት አማካዮች መጫወትን ምርጫቸው ለሚያደርጉት ገብረመድኅን ኃይሌ የአማካይ ክፍልም ጥሩ አማራጭ እንደሚሆን ይጠበቃል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ