“መንግሥት የሚሰጠውን ውሳኔ እየጠበቅን ነው” አቶ ባህሩ ጥላሁን

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቅጥር ዙርያ ቅድሚያ ሰጥቶ ይወያያል የተባለው የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የዛሬው ስብሰባ ውሎ።

የሥራ አስፈፃሚ አባላት የሆኑት ኮሎኔል ዐወል አብዱራሂም፣ አሊሚራህ መሐመድ፣ ሶፊያ አልማሙን እና አብዱረዛቅ መሐመድ ባልተገኙበት ዛሬ ረፋድ 4:00 በፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት በተካሄደው መደበኛ ስብሰባ በዋናነት ይነሳል የተባለው የዋልያዎቹን የአሰልጣኝ ቅጥር ሳይመለከቱት እንዳለፉ እና ይልቁንም ከተጨዋቾች ዝውውር ጋር በተያያዘ መሻሻል ባለባቸው ፖሊሲዎች ዙርያ ትኩረታቸውን አድርገው እንደነበረ ለማወቅ ችለናል።

የአፍሪካ ዋንጫ ሊካሄድ የስምንት ሳምንት ጊዜ ብቻ በቀረበት በአሁኑ ወቅት ከብሔራዊ ቡድን በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ምን ነገር አለ በማለት አቶ ባህሩ ጥላሁንን ጠይቀናቸው ተከታዩን ምላሽ ሰጥተውናል። “በብሔራዊ ቡድን ጉዳይ ለመነጋገር መንግሥት ውድድሩን እንድናደርግ የሚያስችል ፍቃድ እየጠበቅን ነው። መንግሥት በዚህ ዙርያ ምላሽ እስኪሰጠን ድረስ በብሔራዊ ቡድን ጉዳይ ምንም ማለት አይቻልም።”

ካፍ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎችን ማራዘሙን እንዳሳወቀ ሁሉ አሁንም በካፍ በኩል የተለየ ውሳኔ እስካልተሰጠ ድረስ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዋን ጥቅምት ወር መጨረሻ እና ኀዳር መጀመርያ ላይ እንደምታደርግ ማሳወቁ ይታወቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!