ሽመክት ጉግሳ ወደ ቀድሞ ክለቡ ለማምራት ተስማማ

ወላይታ ድቻ የቀድሞው ተጫዋቹ ሽመክት ጉግሳን ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡

በመስመር አጥቂነት በፕሪምየር ሊጉ ከሚጫወቱ ተጫዋቾች መካከል ከግንባር ቀደሞቹ የሚጠቀሰው ሽመክት ከዚህ ቀደም ለትውልድ ከተማው ክለብ ወላይታ ድቻ በቀድሞው ብሔራዊ ሊግ (በአሁኑ አንደኛ ሊግ) የተጫወተ ሲሆን ከዛም በመቀጠል በአየር ኃይል፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ደደቢት እንዲሁም ከ2011 ጀምሮ ደግሞ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በፋሲል ከነማ መለያ ምርጥ የውድድር ጊዜን ካሳለፈ በኃላ በጃኖ ለባሾቹ ቤት ውሉን ለማራዘም የተስማማ ቢሆንም በዛሬው ዕለት ግን ለቀድሞው ክለቡ የሁለት ዓመት ውል ቅድመ ስምምነት ፈፅሟል፡፡

የጦና ንቦቹ ዘጠነኛ ፈራሚ የሆነው ሽመክት በወላይታ ድቻ ቤት ካሉት ወንድሞቹ አንተነህ ጉግሳ እና ቸርነት ጉግሳ ጋር አብሮ የመጫወት ዕድልንም ያገኛል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: