ሲዳማ ቡና ማሊያዊውን አጥቂ ለማስፈረም ተስማማ

ማሊያዊው አጥቂ ማማዱ ሲዲቤ ለሲዳማ ቡና ለመጫወት ተስማምቷል፡፡

የሞሮኮውን ክለብ ራፒድ ኦውድን ለቆ በ2011 ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ነበር በፕሪምየር ሊጉ መጫወት የጀመረው። ይህ ማሊያዊው አጥቂ በጅማ አባጅፋር የአንድ አመት ቆይታን ካደረገ በኃላ ዘንድሮ ሊጉ እስከ ተሰረዘበት ጊዜ ድረስ ለባህርዳር ከተማ በመጫወት ያሳለፈ ሲሆን በቀጣዩ ዓመት ወደ ሲዳማ ቡና ለማምራት ቅድመ ስምምነት ፈፅሟል፡፡

ሲዳማ ቡና ይህ የማሊ ዝግነት ያለው አጥቂ አምስተኛ አዲስ ፈራሚው ሲሆን ከሰንደይ ሙቱኩ፣ በጥር ወር ከመቐለ ቡድኑን ከተቀላቀለው ተከላካይ ላውረንስ ኤድዋርድ እና በቅርቡ ከፈረመው ዩጋንዳዊው አማካይ ያስር ሙገርዋ ቀጥሎ አራተኛ የውጪ ዜግነት ያለውም የክለቡ ተጫዋችም ሆኗል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: