ሲዳማ ቡና የወሳኝ ተጫዋቹን ውል አራዘመ

የመስመር አጥቂው ሀብታሙ ገዛኸኝ በሲዳማ ቡና ለመቆየት ተስማማ፡፡

የወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ውል እያራዘሙ እንዲሁም አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም እየተስማሙ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች የወሳኙን የመስመር አጥቂ ሀብታሙ ገዛኸኝን ውል ለሁለት ተጨማሪ ዓመት ለማቆየት ዛሬ ተስማምተዋል፡፡ 2010 ደቡብ ፖሊስን ለቆ ወደ ሲዳማ ቡና ካመራ በኋላ ያለፉትን ሦስት የውድድር ዓመታት ለክለቡ ወሳኝ ግቦችን ከማስቆጠር ባለፈ ምርጥ ብቃቱን በማሳየት በፕሪምየር ሊጉ ደምቆ ታይቷል፡፡ ተጫዋቹ ውሉን ማጠናቀቁን ተከትሎም በክለቡ ለመቆየት ዛሬ በክለቡ ፅህፈት ቤት ተገኝቶ ውሉን አራዝሟል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: