ከወራት በኋላ የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

የካፍ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዓ ከሦስት ዓመታት በኃላ በድጋሚ በአዲስ አበባ ይደረጋል፡፡

ከትናንት በስቲያ የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የበላይ ሀላፊ የሆኑት ፕሬዝዳንት አህመድ አህመድ ትራንዚት አድርገው አዲስ አበባ ለሠላሳ ደቂቃ ያህል ቆይታ ማድረጋቸው ይታወሳል። በቆዩባታ አጭር ሰአታትም ቢሆን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን በፕሬዝዳንቱ አቶ ኢሳይያስ ጂራ አማካኝነት አቀባበል አድርገውላቸው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሀገሪቱ የእግርኳስ ውድድር ለማስጀመር እያደረገችው ጥረት እና ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ገለፃ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፅህፈት ቤት ሀላፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት የካፍ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔን ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ መመረጧን የካፍ ፕሬዝዳንት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መግለፃቸውን የገለፁልን ሲሆን ጉባዔውም ከአራት ወራት በኃላ ከታህሳስ 1 እስከ 10 ባሉት ቀናት ሊካሄድ ቀጠሮ መያዙንም ኃላፊው ነግረውናል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የፊፋ ዓመታዊ ጉባዔን ከወራት በፊት ለማስተናገድ መሰናዶ አጠናቃ የነበረ ቢሆንም የኮሮና ወረርሽን እንዲሰረዝ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: