አማኑኤል ዮሐንስ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ለመመለስ ተስማማ

ከሳምንታት በፊት ለፋሲል ከነማ ለመጫወት ተስማምቶ የነበረው አማኑኤል ዮሐንስ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ለመመለስ ተስማምቷል።

ከኢትዮጵያ ቡና የታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኃላ ያለፉትን ዓመታት በክለቡ የተከላካይ አማካይ ቦታ ላይ ምርጥ ብቃቱን አሳይቷል፡፡የክለቡ አምበልም ጭምር በመሆን ሲያገለግል የነበረው አማኑኤል አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ወደ ክለቡ ከመጣ በኃላ የመከላከል ሚናም ተሰጥቶት ሲጫወት የነበረ ሲሆን ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ፋሲል ከነማ አምርቶ በሁለት ዓመት ውል ለመጫወት ቅድመ ስምምነት እንደተፈራረመ የጎንደሩ ክለብ ገልፆ ነበር፡፡ ሆኖም ተጫዋቹ በድጋሚ ወደ ቡናማዎቹ ቤት እንዲመለስ በተደረገው የማግባባት ስራ በድጋሚ ወደ ልጅነት ክለቡ በመመለስ የአራት ዓመት ቅድመ ስምምነት ፊርማን አኑሯል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: