ፕሪምየር ሊጉ ለቀጥታ የሬድዮ ስርጭት ሊሸጥ ነው

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን በሬድዮ በቀጥታ ለማስተላለፍ ለሚፈልጉ ድርጅቶች ሊሸጥ ነው፡፡


*መረጃው ኢፊዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ነው።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አ/ማ የኢትዮጵያን ፕሪምየር ሊግ ውድድርን ለመምራት የተቋቋመ ህጋዊ ተቋም ነው። ኩባንያው በ2013 በጀት ዓመት በሀገራችን የሚካሄደውን በሜዳ እና ከሜዳ ውጪ የፕሪምየር ሊግ ውድድር በሬድዮ የቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ ለሚፈልጉ የሚዲያ ተቋማት ሊሸጥ መሆኑ ታውቋል ፡፡

በመሆኑም ሊግ ኩባንያው በቀጣይ የሚካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በቀጥታ የሬድዮ ስርጭት ለማስተላለፍ ህጋዊ ፍቃድ ለአላቸው ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ የሚዲያ ተቋማት ለመሸጥ በሚቀጥለው ሳምንት ጨረታው እንደሚወጣ ለማወቅ ተችሏል ፡፡

ሊግ ኩባንያው ቀደም ሲል የሊግ ውድድሩን የቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት እና የውድድር ስያሜ ሽያጭ ጨረታ አውጥቶ አሸናፊውን ለመለየት በሒደት ላይ መሆኑ ይታወቃል። የሚያገኘው ገቢ የኩባንያው እና የተወዳደዳሪ ክለቦችን ፋይናንሻል አቅም ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: