ወልቂጤ ከተማዎች የአጥቂ መስመር ተጫዋች ለማስፈረም ተስማምተዋል

በወላይታ ድቻ ውሉን ለማራዘም ተስማምቶ የነበረው የአጥቂ መስመር ተጫዋች በዛሬው ዕለት ለወልቂጤ ከተማ ለመጫወት ተስማምቷል።

የቀድሞው የስልጤ ወራቤ፣ መከላከያ ፣ ሲዳማ ቡና እና ወላይታ ድቻ ተጫዋች ዓምና ሊጉ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ 9 ግቦችን አስቆጥሮ 1 ግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ በማቀበል ጥሩ ጊዜ ካሳለፉ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቾች አንዱ መሆን ችሎ ነበር። ይህን ተከትሎ ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር ከተያያዘ በኋላ ከሳምንታት በፊት በወላይታ ድቻ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ለመጫወት ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም የሠራተኞቹ አዲስ ፈራሚ ለመሆን ተስማምቷል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!