ከፍተኛ ሊግ | የካ ክፍለ ከተማ የአሰልጣኙን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዘመ

አሰልጣኝ ባንተይርጋ ጌታቸው ለዘጠነኛ ዓመት በየካ ክፍለ ከተማ ለመቆየት ውሉን አራዘመ፡፡

በኢትዮጵያ እግርኳስ በአንድ ክለብ ውስጥ ለረዥም ጊዜ መቆየት ፈታኝ ቢሆንም አሰልጣኝ ባንተይርጋ ጌታቸው የካ ክፍለ ከተማን ከምስረታው 2005 አንስቶ እያሰለጠነ ይገኛል፡፡ በአንደኛ ሊግ ጀምሮ ያለፉትን ሦስት የውድድር ዓመታት ደግሞ በከፍተኛ ሊጉ በአሰልጣኝነት እየመራ የሚገኘው አሰልጣኝ ባንተይርጋ ጌታቸው ከአንድ ወር በፊት ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ለተጨማሪ አንድ ዓመት አሁንም በክለቡ ለመቆየት ከስምምነት መድረሳቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ከአሰልጣኙ እና ክለቡ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: