የደቡብ ፖሊስ ተጫዋቾች ለሁለተኛ ጊዜ ቅሬታቸውን አሰምተዋል

የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ደቡብ ፖሊስ ተጫዋቾች የደመወዝ ይከፈለን የቅሬታ ደብዳቤን ለፌዴሬሽኑ አስገብቷል፡፡

ቁጥራቸው በርከት ያለ የክለቡ ተጫዋቾች በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት “የሀምሌ እና ነሐሴ ወር ደመወዝ ሊሰጠን እየተገባ ክለቡ ምንም ክፍያ አንፈፅምም ብሎናል። በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበንም መልስ አላገኘነም። መፍትሔ ስላላገኘን በህግ አግባብ መሄድ ጀምረናል” ብለዋል። የክለቡ ፕሬዝዳንት ኢንስፔክተር እታገኝ ዜና በበኩላቸው ” የአንድ ወር ደመወዝ ብቻ ነው የምንፈፅመው። በኮሮና ቫይረስ ክፍተት ስለተፈጠረ ነው። የሁለት ወር ደመወዝ የሚባለውን እኛ አናውቅም።” በማለት ምላሽ ሰጥተውናል፡፡

ከሳምንት በፊት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተጫዋቾቹ እና የክለቡ አሰልጣኞች ተፈራርመው ለፌዴሬሽኑ የክስ ደብዳቤን ያስገቡ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የመጨረሻ ያሉትን ደብዳቤ ለደቡብ ፖሊስ ክለብ ማስገባታቸውን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ከወርሀዊ የደመወዝ ክፍያ ጋር በርካታ ክለቦች ቅሬታን እያስተጋቡ ሲሆን ከደቡብ ፖሊስ ሌላ ቁጥራቸው ስድስት የሚሆን የከፍተኛ ሊግ ክለብ ተጫዋቾች ለፌዴሬሽኑ የይከፈለን ደብዳቤን ማስገባታቸውን ከፌዴሬሽኑ መረጃን አግኝተናል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: