ሁለት ክለቦች በአፍሪካ መድረክ እንዲሳተፉ ተወሰነ

በዛሬው የሊግ ኩባንያው የውይይት መድረክ ኢትዮጵያ በአፍሪካ መድረክ መወከል አለባት በሚል በተሰጠ አብላጫ ድምፅ ሁለት ክለቦች መወከላቸው ተገለፀ፡፡

በሀገራችን የኮሮና ወረርሺኝ ከገባ ጊዜ አንስቶ ውድድሮች መቋረጣቸው ይታወሳል፡፡ የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ17ኛው ሳምንት ላይ በመቋረጡ ኢትዮጵያን በአፍሪካ መድረክ የሚወክል ክለብ አይኖራትም፤ ለዚህም የሚረዳ ህግ የለም በሚል መወሰኑ የሚታወስ ነው። ሆኖም በዛሬው የጉባዔው ሁለተኛ ቀን ውሎ ኢትዮጵያ ሁለት ክለቦች በአፍሪካ መድረክ የሚወክሉ ክለቦችን እንዲኖሩ በአብላጫ ድምፅ በማፅደቅ ተጠናቋል፡፡ በዚህ መሠረት መቐለ 70 እንደርታ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ፋሲል ከነማ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተወስኗል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!