የፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ኮሚቴ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ጥያቄ አቀረበ

የፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ በአሰልጣኝ ቅጥር ዙርያ የተጠየቀውን ምክረ ሀሳብ አቅርቦ ውድቅ የተደረገበት ቴክኒክ ኮሚቴ ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጥ ነው።

አወዛጋቢው የሰሞኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአሰልጣኝ ሹም ሽርን አስመልክቶ የተለያዩ ጉዳዮች እየተነሱ መሆናቸው ይታወቃል። የዚህ ጉዳይ መሪ ተዋንያን በመሆን የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምክረ ሀሳብ እንዲያቀርብ ተጠይቆ ባለ ዘጠኝ ነጥብ ሰነድ በሙሉ ድምፅ ተፈራርሞ በቃለ ጉባዔ አፅድቀው ለፌዴሬሽኑ ማቅረባቸውን መግለፃችን ይታወሳል። ሥራ አስፈፃሚውም የቀረበለትን መነሻ ከሰፊ ውይይት በኃላ ምክረ ሀሳቡን በድምፅ ብልጫ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ መደረጉ ይታወቃል። ይህ ለምን ሆነ? መጀመርያስ ለምን ምክረ ሀሳብ እንድንሰጥ ተጠየቅን በሚል ቅር የተሰኘው ስድስት አባላት ያሉበት ቴክኒክ ኮሚቴ ያለውን እውነታ ለስፖርት ቤተሰቡ በዝርዝር ለማቅረብ በማሰብ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት እንደፈለጉ ለማወቅ ችለናል።

ይህን ተከትሎም ፌዴሬሽኑ ጊዜ፣ ቦታ አዘጋጅቶ እና ቀኑን ወስኖ ለመገናኛ ብዙኀን ጥሪ እንዲያደርግላቸው ጥያቄ አቅርቧል። ይሁን እንጂ ፌዴሬሽኑ ጥያቄውን ተቀብሎ ጥሪ የማያደርግለት ከሆነ ቴክኒክ ኮሚቴ በራሱ መንገድ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት እንዳሰበ ሰምተናል።

በቀጣይ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚሰሙ አዳዲስ ነገሮች ካሉ ተከታትለን የምናቀርብ መሆኑን እናሳውቃለን።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!