አብርሃም መብራቱ የአንድ ክለብ ጥያቄ ሳይቀበሉ ቀርተዋል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለብ የአሰልጥንን ጥያቄ የቀረበላቸው የቀድሞ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ጥያቄውን ሳይቀበሉ እንደቀረ ተሰማ።

በቅርቡ ኮንትራታቸው መጠናቀቁን ተከትሎ ይቀጥላሉ አይቀጥሉም በሚል በብዙ ውዝግብ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር እንደማይቀጥሉ የተረጋገጠው የአሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ የሰበታ ከተማ እግርኳስ ክለብ አሰልጣኝ እንዲሆኑ የቀረበላቸውን ጥያቄ ሳይቀበሉ ቀርተዋል። በብሔራዊ ቡድን ጥሪ አሰልጣኝ ውበቱ አባተን ያጡት ሰበታዎች በምተኩ ከብሔራዊ ቡድን የተሰናበቱትን አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱን መተካት ቢፈልጉም እርሳቸው ግን እረፍት ማድረግ እንደሚፈልጉ እና ለተወሰኑ ጊዚያት ወደ አሰልጣኝነቱ እንደማይገቡ በመግለፃቸውን ሰበታ ያቀረበው ጥያቄውን እንዳልተቀበሉ ሰምተናል።

ከዚህ ቀደም ከአንድ ወር በፊት ገደማ አሰልጣኝ አብርሃም በታንዛኒያው ሀያል ክለብ ያንግ አፍሪካ ከተፈለጉ ትልልቅ አስር አሰልጣኞች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸው ቢነገርም በስተመጨረሻ ያንጋ ከአውሮፓ አሰልጣኝ መሾሙ ይታወቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: